Skip to form

District of Columbia Public Schools

enroll@k12.dc.gov

1200 First St NE Washington, DC 20002

Document Signers
  • 1 Parent/Guardian

  • 2 School Official

SeamlessDocsከዲሲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ጋር በመሆን፣ ለ2020-2021 የትምህርት ዓመት እንኳን ደህና መጣችሁ! የተማሪዎቹ የቀድሞ መነሻቸው ወይም ሁኔታቸው ምንም ሆነ ምን፤ እያንዳንዱ ትምህርት ቤቶቻችን ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ ትምህርት በመስጠት ሁሉም ተማሪዎች ለኮሌጅ፣ ለስራ መስክ እና ለሕይወት ስኬት መዘጋጀታቸውን ለማረጋገጥ፣ DCPS ጥረት ያደርጋል። ሁሉንም ተማሪዎች ማገልገላችን፣ ክብርና ደስታን የሚያጎናጽፍ ነገር ሲሆን፣ ሌላ ግሩም የሆነ የትምህርት ዓመት እንዲገጥመን በጉጉት እንጠብቃለን። የኢሚግሬሽን ሁኔታቸው ወይም ዜግነታቸው ምንም ሆነ ምን፣ DCPS በሕዝብ ትምህርት ቤት ውስጥ ገብተው የሚማሩን የእያንዳንዱን ተማሪዎችን መብት ለመጠበቅ ይተጋል። ከዚህም ጋር በተያያዘ፣ ብቁነታቸው የተረጋገጠ የኮሎምብያ ዲስትሪክት ነዋሪዎች ሁሉ፣ ስለተማሪዎች ወይም ቤተሰቦቻቸው የኢሚግሬሽን ሁኔታ ሳይጠይቅ፣ በትምህርት ቤቶቹ ውስጥ ገብተው እንዲማሩ፣ DCPS ይፈቅድላቸዋል።

እባክዎን ያስተውሉ: በዚህ እንከን የለሽ ሰነድ (SeamlessDocs) ላይ፣ ቅጹ አጠናቀው ሞልተውና ለማስገባት እንዲችሉ፣ የኢሜል አድራሻ ያስፈልጋል። የኢሜል አድራሻ ከሌለዎት፣ እባክዎን የትምህርት ቤትዎን የምዝገባ ቡድን ያነጋግሩ

ለትምህርት ዓመት 2020-2021 በDCPS ለመመዝገብ፣ ሁሉም ቤተሰቦች ከዚህ በታች የተመለከቱትን የእርምጃ ደረጃዎች ማጠናቀቅ አለባቸው:
1. የደብዳቤውን የመጀመሪያ ገጽ ሙሉ በሙሉ ያንብቡ: የደብዳቤው የመጀመሪያ ገጽ (cover letter)፣ ምዝገባውን እንዴት መሙላት እንደሚችሉ እና የSY20-21 የምዝገባ ጥራዝዎን (packet) ለማስገባት ምን ዓይነት ሰነዶች እንደሚያስፈልግዎት፤ ጠቃሚ የሆነ መረጃዎችን አካቶ ይዟል።

2. ሁሉንም የተጠየቁትን፤ የሚፈለጉ እና የሚመለከተውን መረጃዎች ይሙሉ።
 • አንብበው ማጠናቀቅ ያለብዎት፣ 7 (ሰባት) ገጾች አሉ።
 • አስፈላጊ የሆኑት መረጃዎች በሙሉ፣ ኮከብ (አስተሬክስ) ምልክት (*) ተደርጎባቸው ተለይተዋል።
 • በቅጹ ላይ የሚገኘውን ከሞሉ በኋላ፤ እንደገና ትክክለኛነቱን ደግመው ተመልከተው ሙሉ በሙሉ ካልጨረሱ በስተቀር፣ በቅጹ ላይ የሚገኘውን “Signature Here” የሚለውን አማራጭ አይምረጡ። ከመፈረምዎ በፊት ሁሉንም 7 (ሰባት) ገጾች ተመልክተው እና አጠናቀው መጨረስ አለብዎት።
 • ጥራዙን (packet) አጠናቆ ለመጨረስ ጊዜ ከሌለዎት፣ ከታች ከስክሪኑ (screen) እግርጌ በሚገኘው የጽሁፍ ሰሌዳ (banner) ላይ የሚገኘውን “Save and Continue Later” የሚለውን አማራጭ ይምረጡ። ይህም በSeamlessDocs ውስጥ፣ አካውንት እንዲፈጥሩ ያደርግዎታል።
3. ከታች በስክሪኑ (screen) የጽሁፍ ሰሌዳ (banner) ላይ የሚገኘውን የመጨረሻውን Submit and Sign” የሚለውን ቁልፍ (button) መምረጥ

4. ቅጾቹን ከፈረሙ በኋላ፣ የሚመለከተውን አባሪዎች (attachments) እንዲጭኑ (upload እንዲያደርጉ) ይጠየቃሉ።
 • አዲስ ተማሪዎች፣ አንድ የዕድሜ ማረጋገጫ ሰነድ ማስገባት አለባቸው። ተቀባይነት ያላቸው የዕድሜ ማረጋገጫ ሰነዶች፤ በምሳሌነት ከተካተቱት ውስጥ ̶ የልደት የምስክር ወረቀት፣ የሆስፒታል መዝገቦች፣ የቀድሞ ትምህርት ቤት ሰነዶች፣ ፓስፖርት(passport) ወይም የጥምቀት የምስክር ወረቀት ናቸው።
 • ሁሉም የዲሲ ነዋሪዎች፣ ነዋሪነታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው። ተቀባይነት ያለው የዲሲ የነዋሪነት ሰነዶች እዚህ ሊገኙ ይችላሉ።
 • ጥራዙን (packet) ሞልተው ለማጠናቀቅ ከመጀመርዎ በፊት፣ ሁሉንም ሰነዶችዎን ለመጫን (upload) ለማድረግ እንዲያሰናዱ እናበረታታዎታለን።
 • ምስሎችን (pictures) ጨምሮ፤ የተለያየ የይዘት አቀራረቦች (formats) ያላቸው ሰነዶች ሊጫኑ (upload ሊደረጉ) ይችላሉ።

5. የኤሌክትሮኒክ ፊርማ ለመፍጠር የሚያግዘውን ትዕዛዝ በመከተል እና በጥራዙ ላይ በሚፈለገው በ6 (ስድስት) ቦታዎች ላይ ፊርማዎን ያኑሩ።
 • የሚከተለው በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ዓረፍተ ነገር፣ ምልክት ማድረጊያው (checkmark) ላይ ምልክት ማድረግ እንዳለብዎት እባክዎን ያስተውሉ: “I agree to electronically sign and to create a legally binding contract between the other party and myself, or the entity I am authorized to represent.” መልዕክቱ የሚገልጸው: “[የኤሌክትሮኒክ ፊርማ ለመፈረም እና በእኔ እና በሌላኛው ወገን መካከል ወይም ወክዬው ለመቅረብ ስልጣን ለተሰጠኝ አካል፤ ሕግ የሚያስገድደው ውል (ኮንትራት) ለመፍጠር ተስማምቻለሁ]።”
6. ፊርማዎን በሚፈለጉት ቅጾች ላይ ካስገቡ በኋላ፣ Finalize and Submit” የሚለውን ይምረጡ።

7. ሌላ ማን ይህን ሰነድ ሊፈርም እንደሚያስፈልገው (Who Else Needs to Sign this Document)፣ ይጠየቃሉ፤ ከዚያም በኋላ፣ ወደታች ከሚዘረዘረው (drop-down ) ምርጫ፣ ምዝገባውን የሚሞሉበትን ትምህርት ቤት ይምረጡና፣ “Continue” የሚለውን ተጭነው፣ የምዝገባ ጥራዙን (packet) ያስገቡ።

አንዴ ካስገቡት በኋላ፣ ያስገቡት ጥራዝ (packet) ቅጂ/ኮፒ ይደርስዎታል። ከዚህ በኋላ ትምህርት ቤቱ ያስገቡትን ይመለከታል፣ እንደአስፈላጊነቱ ከእርስዎ ጋር ክትትል ያደርጋል፣ እና ጥራዙን (packet) ይፈርማል፤ ይህም ምዝገባው መጠናቀቁን ያመላክታል። ከዚህ በኋላ በትምህርት ቤቱ የተፈረመበት ሌላ ቅጂ/ኮፒ ያገኛሉ። ምዝገባዎ እስከመጨረሻ እንደተጠናቀቀ የሚቆጠረው፣ ቅጽዎትን ትምህርት ቤቱ በህጋዊነት ከፈረመ እና ይህ መከናወኑን የሚያረጋግጥ ኢሜል ሲደርስዎ ነው። በዚህ መድረክ ላይ የተሰበሰበው መረጃ፣ ለምዝገባው ዓላማዎች ብቻ የሚውል መሆኑን እባክዎን ይወቁ።

ይህ አዲስ ሂደት፣ ለትምህርት ቤቶች እና ቤተሰቦች አገልግሎት በስራ ላይ እንዲውል በምናካሂደው እንቅስቃሴዎች ሁሉ ስለታገሳችሁን እናመሰግናለን። ማንኛውም ጥያቄዎች ካለዎት፣ እባክዎን ትምህርት ቤትዎን ወይም የDCPS የምዝገባ ቡድንን፣ በenroll@k12.dc.gov ያነጋግሩ
Please check that you agree before continuing.
የሰነዱ(ዶቹ)ን ዲጂታል ስሪትን (version) በፍቃደኝነት ለማጠናቀቅ እና በመጠቀሚያ ክፍለጊዜዬ ውስጥ ያለው መረጃ ተከማችቶ እንደሚቀመጥ አውቄ፣ ይህን በመቀጠል፤ መስማማቴን ገልጫለሁ።
Signature HereClick to Sign
03/01/2021Click to Sign
_______
Signature HereClick to Sign
03/01/2021Click to Sign
Signature HereSchool Official Will Sign Here
03/01/2021
_______
_______
Signature HereClick to Sign
03/01/2021Click to Sign
Signature HereClick to Sign
03/01/2021Click to Sign
Signature HereClick to Sign
03/01/2021Click to Sign
_______
Signature HereClick to Sign
03/01/2021Click to Sign

Create Your Signature

Please fill in your name and email and then either draw or type your signature below.

x

Signature Type

Type Draw Upload Custom
Clear Signature

Signature will be applied to the page. You will have a chance to review after signing.

Check this box to continue

x

Additional Signatures Required

የተማሪ ዕድሜ ማረጋገጫ Click Here to Upload
የነዋሪነት ማረጋገጫ 1 Click Here to Upload
የነዋሪነት ማረጋገጫ 2 Click Here to Upload
የነዋሪነት ማረጋገጫ 3 Click Here to Upload
የነዋሪነት ማረጋገጫ 4 Click Here to Upload